ስለ-እኛ
ህፃናት ጥሩ የሆነ ለህይወታቸው መሰረት ለመጣል የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ዙርያ ለሚቀጥለው የመደበኛ ት/ት ፕሮግራም የተለያዩ አገልግሎቶችን በጥራት በአቅርቦትና በፍትሀዊ ሥርጭት እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት፤ በዕውቀትና በክህሎት የታነፀ ለፈጠራ ና ለምርምር የተዘጋጀ በአንድነት ላይ የተገነባ አግባብነት ያለውን ሥርዓት የተጎናፀፈ መስራች ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል የአፀደ-ህፃናት ት/ት ፕሮግራም ማቅረብ ነው፡፡ ለጀማሪ ህፃናት የሚሰጠውን መሠረታዊ የሆነ የቅድመ ቋንቋ፣ ፅሁፍ፤ ቅድመ-ስሌት አካባባዊና ማህበራዊ ግንዛቤና የሥነ-ሥርዓትን/ግብረ-ገብነት ችሎታዎችን ለማዳበር እንዲችሉ ማስቻል ነው
ስትራቴጂካዊ ግቦች
ለህፃናት እንክብካቤና ቅድመ መደበኛ ት/ት ፕሮግራም ወጥ የሆነ ከመንግስት መዋቀር ጋር ተዛማች የሆነ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ውስጥ መካተታቸውን ማረጋገጥ
የፕሮግራሙን አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር፡፡
ት/ት ሚኒስቴር ካዘጋጀው ስታንዳርድ ጋር የተጣጣመና ጥራቱን የጠበቀ የህፃናት ክብካቤና አፀደ-ህፃናት ት/ት ጋር የተያያዘውን ሥርዓት ተከትሎ መመሪያዎችን መተግበር እንደ- አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መተርጎም፡፡
ህፃናት በየዕድሜያቸው በተዘጋጀላቸው ዕቅድና ፕሮግራም መነሻነት የቀረቡላቸውን የት/ት ይዘቶች እንዲዘጋጁ ማስቻል፡፡